Registrations Closed
National Mission Summit
እንኳን ወደ ኢቫሱ የብሔራዊ ጉባኤዎች መመዝገቢያ ቅጽ በደህና መጡ
ስለ ፕሮግራሞቹ፡ የኢቫሱ ዋና አላማ ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት ነዉ፡፡ ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ ኢቫሱ ልዩ ልዩ ስልቶችን የሚጠቀም ሲሆን አገልጋይ መሪዎችን ማብቃት ከስልቶቹ አንዱ ነዉ፡፡ ብሔራዊ የመሪዎች ጉባኤ በሃገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተማሪ ህብረት መሪዎችን ለማስታጠቅ እና አቅጣጫ ለመስጠት የሚሰበሰብ ጉባኤ ሲሆን፤ ብሔራዊ የተልእኮ ጉባኤ ደግሞ የወንጌል ስራ በሰፊዉ ይሰራ ዘንድ በወንጌል ዙሪያ የሚሰሩ ልዩ ልዩ የተማሪ አስተማባሪዎችን ለማስታጠቅና አቅጣጫ ለመስጠት የሚሰበሰብ ጉባኤ ነዉ፡፡
የምዝገባ ዝርዝር መረጃ
ብሔራዊ የተልእኮ ጉባኤ(National Mission Summit)
ቀን፡ ሰኔ 29 - ሐምሌ 04/ 2018 (July 6 - 11/2026) ተማሪዎች የሚገቡት ሰኞ ሰኔ 29 ሲሆን፤ ቅዳሜ ሐምሌ 04 የሚወጡበት ቀን ይሆናል፡፡
ቦታ- ደብረዘይት
የተሳታፊ ተማሪዎች ኮታ:
- ከየግቢዉ 3 የወንጌል ስርጭት አስተማባሪ መሪዎች ፣
- 2 የማህበራዊ አገልግሎት አስተማባሪ መሪዎች እና
- 2 ዲጂታል/ ሚድያ ቡድን መሪዎች
- የንዑስ ቡድን አስተባባሪዎች
የመመዝገቢያ ክፍያ: ለመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም ለግል ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች - 1000 ብር
የተሳታፊ ተማሪዎች ምዝገባ ማብቂያ ቀን፡ ሰኔ19/2018 (June 26/2026)